Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 3ኛው ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የ3ኛ ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ መሰጠት ተጀምሯል፡፡
ክትባቱ ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዕድሜያቸው12 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆናቸው ሁሉ በሁሉም የመንግስት ጤና ጣቢያዎችና በተመረጡ ጊዜያዊ መስጫዎች በዘመቻ መልክ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡
በዚህ የክትባት ዘመቻም 249 ሺህ የሚሆን የክትባት ዶዝ ለመስጠት መታቀዱ ተገልጿል፡፡
ኮቪድ 19 አሁንም የህብረተሰቡ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የሥነልቦና ተጽዕኖ እያሳደረ በመሆኑ ይህንን ተጽእኖ ለመቀነስ ክትባቱን መውሰድ እንደሚገባ መገለፁን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.