Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 76 ሺህ ህጋዊ የመሬት ይዞታዎችን መመዝገብና ማረጋገጥ መቻሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ  76 ሺህ ህጋዊ የመሬት ይዞታዎችን መመዝገብ እና ማረጋገጥ መቻሉን የፌዴራል ከተማ መሬት እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው በሀገር አቀፍ ደረጃ ህጋዊ የመሬት ይዞታዎችን መመዝገብ እና ማረጋገጥ ወይም የካዳስተር ስርአትን እየዘረጋ ሲሆን ፥ በዚህ አመት በመዲናዋ ያከናወነው ስራ ውጤታማ መሆኑን የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን የስራ ሀላፊ አቶ አራጌ ክብረት ለፋናብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ በ6 ወሩ የተከወነው ስራ ከእቅዱ አንፃር ሲታይም አፈፃፀሙ 92 ከመቶው ነው።

የካዳስተር ስርአቱ በኦሮሚያ ፣ አማራ፣ ደቡብ ፣ ትግራይ፣ ሀረሪ ክልሎች እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን፥ አፈፃጸሙ ግን 8 ከመቶ ብቻ መሆኑን ነው አቶ አራጌ የተናገሩት።

ለዚህም በክልሎች ለታየው ዝቅተኛ አፈፃፀም የግብአት እጥረት፣ ለዘርፉ ትኩረት አለመስጠት እና በቅንጅት አለመስራት በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።

በቀጣይ እነዚህ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ ይሰራል ነው የተባለው።

 

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.