Fana: At a Speed of Life!

በሩብ ዓመቱ 12 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 336 የዳያስፖራ ባለሃብቶች የምልመላና የድጋፍ አገልግሎት ተሰጥቷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጀመሪያ ሩብ ዓመት 12 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 336 የዳያስፖራ ባለሃብቶች የምልመላና የድጋፍ አገልግሎት መስጠቱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማውን በቢሾፍቱ ከተማ አካሂዷል፡፡
በዚህ ወቅት ለዳያስፖራ ባለሃብቶች የምልመላና የድጋፍ አገልግሎት ከመሰጠቱ ባሻገር 825 ዳያስፖራዎች የውጭ ምንዛሪ ደብተር እንዲከፍቱ በማድረግ ከ1 ሚሊየን ዶላር በላይ ተቀማጭ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።
ዳያስፖራውን በማስተባበር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ32 ሚሊየን ብር በላይ፣ ለገበታ ለሃገር ከ16 ሚሊየን ብር በላይ እንዲሁም ለኮቪድ-19 መከላከያ ከ194 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ መቻሉ ተነግሯል፡፡
በመድረኩ የቀጣይ ሁለት ወራት የስራ ክፍሎች ቼክሊስትና የዳያስፖራ ማህበረሰብ ልማት ሰነድ ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.