Fana: At a Speed of Life!

በመጋቢት ወር ከ320 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጋቢት ወር ብቻ 320 ሚሊየን 427ሺህ 726 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢ እና የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችና ሕገ-ወጥ ገንዘቦች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከነዚህም ውስጥ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች የ235 ሚሊየን 543ሺህ 640 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ሲሆን ሊወጡ ሲሉ የተያዙት ደግሞ 84 ሚሊየን 884ሺህ 86ብር ተገምተዋል፡፡
ይህም በበጀት ዓመቱ መጋቢት ወር ከተያዘው ዕቅድ አንፃር 144 በመቶ አፈጻጸም ተመዝግቧል ነው የተባለው፡፡
ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ72 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቧል ተብሏል፡፡
አዲስ አበባ አየር መንገድ ፣ ሀዋሳ፣ ጅጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሞያሌ፣ ባህርዳር፣ ጋላፊ፣ ፣ ጅማ፣ አዳማ፣ አዋሽ፣ ኮምቦልቻ እና አሶሳ ደግሞ የኮንትሮባንድ እቃዎቹ የተያዙባቸው የጉምሩክ ቅርንጫፎች መሆናቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.