Fana: At a Speed of Life!

በመጪዎቹ 10 ዓመታት ሁሉንም ወረዳዎች በአስፓልት መንገዶች ለማገናኘት እቅድ መያዙ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በመጪዎቹ 10 ዓመታት  ሁሉንም ወረዳዎች በአስፓልት መንገዶች ለማገናኘት እቅድ መያዙን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያገኛኑ መንገዶች ግንባታ ለማከማወንም በመሪ እቅዱ ትኩረት መደረጉ ነው የተነገረው።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በ10 ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ ላይ እየተወያየ በሚገኘበት መድረክ ላይ እቅዱን አቅርቧል።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው ውይይት ላይ የ10ሩ ተጠሪ ተቋማት እቅድ እየቀረበ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።

የመሪ ልማት እቅዱ ውይይት በተጀመረበት በዛሬ እለትም  የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በሀገሪቱ ያሉ ሁሉንም ወረዳዎች በአስፋት መንገድ ለማገናኘት እና  ወደ ጎረቤት ሀገራት ከተሞች የሚደረግን ጉዞ የሚያቀላጥፍ 21 መንገድ ግንባታ ለማከናወን ማቀዱን አስታውቋል ።

በዚህም በዘርፉ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች የስራ እድል ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የመንገድ ዘርፉ ለኢኮኖሚው ትልቅ ድርሻ ያላቸውን የግብርና፣ የነዳጅ፣ የቱሪዝም እና የኢንዱስትሪ ዘርፎች የሚደግፍ ስራ ትኩረት እንደሚሰጠው ተገልጿል።

የመሪ የልማት እቅዱ ውይይት ለፕላን ኮሚሽን ግብረ መልስ ግብዓት እንደሚሰበሰብበት ነው የተነገረው።

በሀይማኖት እያሱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.