Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ለህልውና ዘመቻው ከ25 ሺህ ኩንታል በላይ ስንቅ መዘጋጀቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሴቶች አደረጃጀት ለህልውና ዘመቻው ከ25 ሺህ ኩንታል በላይ ስንቅ መዘጋጀቱ ተገለፀ፡፡

25 ሺህ 510 ኩንታል ስንቅ ለወገን ጦር መዘጋጀቱን የተናገሩት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሀላፊና የማህበረሰብ ስንቅ ሰብሳቢ ወይዘሮ ቀኑ ቢያድጎ በተለያዩ የሴቶች አደረጃጀት እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን አስረድተዋል።

ለተፈናቃዮች የሚውል 300 ኩንታል የተለያዩ አልበሳት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሰብሰቡ የተገለፀ ሲሆን፥ ለተፈናቃዮች 34 ሺህ 426 ኩንታል የምግብ እህል ተዘጋጅቷል ተብሏል።

ሀብት አሰባሳቢ ኮሜቴው በተጨማሪም 3 ሺህ 672 በግና ፍየል 430 ሰንጋዎችን ለወገን ጦር ወደ ግንባር መላኩ ተመላክቷል።

በአይነት የተሰበሰበው ሀብት በጥቅሉ 12 ሚሊየን 476 ሺህ ብር የሚገመት መሆኑን ሀላፊዋ በሰጡት መግለጫ አንስተዋል።

የትግራይ ወራሪ ቡድን እስኪቀበር ድረስ የሚደረገው ድጋፍ በተጠናከረ መንገድ ይቀጥላል ያሉት ሀላፊዋ÷ በቅርብ እየተመዘገበ ያለዉ ድል ሰፊ መነሳሳትን ፈጥሯልም ብለዋል።

በተመሳሳይ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ለመከላከያ ሠራዊት የሚዉል ስንቅ አዘጋጅተዋል፡፡

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተማሪዎችና ሰራተኞች ለመከላከያ ሠራዊት ደጀን ለመሆን ያሳዩትን ተነሳሽነት አድንቀው÷ ኢትዮጵያ ላትመለስ ወደ ፊት የምትገሰግስበት ጊዜ ቅርብ ነው፤ ይህንን እውን ማድረግ የምንችለው አንድ ሆነን ጠንክረን በመማር እና በመሥራት ነዉ ብለዋል፡፡

በምናለ አየነው ፣ ተጨማሪ መረጃ ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.