Fana: At a Speed of Life!

በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ድጋፍ እንዲደረግ ዶክተር ቴድሮስ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን እንዲደግፍ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጥሪ አቅርበዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት፣ የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ወርርሽኙ በታዳጊ ሀገራት የሚያደርሰውን ችግር ለመቅረፍ ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ነው ዋና ዳይሬክተሩ የጠየቁት።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ አራት ወር ማስቆጠሩን ተከትሎ የመዛመት ፍጥነቱና አለም አቀፋዊ ስጋቱ ከፍ ያለ መሆኑ እንዳሳሰባቸው የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገልጸዋል።

ታዳጊ ሃገራት በዚህ ወቅት ዜጎቻቸውን ለመደገፍ ስለሚቸገሩ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሀገራቱን እንዲደግፍ ነው ዶክተር ቴድሮስ ጥሪ ያቀረቡት።

በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ኢኮኖሚ ለመደገፍ እና ቀውስ እንዳያጋጥማቸው አኮኖሚያቸውን ለማገዝ እየሰራን ነውም ብለዋል።

በተመሳሳይ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት በኮሮና ቫይረስ የሚያዙሰወች ቁጥር 1 ሚሊዮን ይደርሳል ያለው ድርጅቱ በቫይረሱ ህይወታቸው የሚያልፍ ሰወች ቁጥርም ወደ 50 ሺ ከፍ እንደሚል ተጠቅሷል።

እስካሁን በ205 አገራት ከ47 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ ከ938 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸውን መረጃወች ያመላክታሉ።

ምንጭ፦ ሲጂቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.