Fana: At a Speed of Life!

በምርት አቅርቦትና ስርጭት ላይ በሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምርት አቅርቦት እና ስርጭት ዙሪያ በሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የንግድ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በአቅርቦትና በስርጭት በኩል ባሉ ችግሮች ዙሪያ ከምርትና አገልግሎት አቅራቢዎች፣ አምራቾች እና አከፋፋዮች ጋር እየመከሩ ነው።

በውይይት መድረኩ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበልን ጨምሮ የአዲስ አበባ ንግድና እንዱስትሪ ቢሮ አመራሮች ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅትም የንግዱ ማህበረሰብ ከትርፍ ይልቅ ዜጋን እና ሀገርን ታሳቢ በማድረግ ምርቶችን በተገቢው ሁኔታ ለህብረተሰቡ ተዳራሽ ማድርግ እንደሚገባው ተመላክቷል።

የኮሮናቫይረስ በሀገሪቱ መከሰቱን ተከትሎ ተለያዩ ሸቀጦች ላይ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ የንግዱን ማህበረሰብ በማይወክሉ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ሲወሰድ መቆየቱም ተገልጿል።

ይሁን እንጂ እርምጃ መውሰድ ብቻ በሀገሪቱ በስፋት የሚስተዋለውን አላስፈላጊ የሸቀጦች ዋጋ መናር መፍታት እንደማይቻል ነው የተገለጸው።

በዚህ መሰረትም በምርት አቅርቦትና ስርጭት ላይ ባሉ ችግሮች ዙሪያ መንግስት ከአምራችና አቅራቢዎች ጋር በጋራ በመሆን መሰራት በሚገባቸውና መወሰድ በሚገባቸው መፍትሄዎች ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በትዝታ ደሳለኝ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.