Fana: At a Speed of Life!

በምርጫው ወቅት የሕግ አስከባሪ አካላት ሰብዓዊ መብቶችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምርጫው ወቅት የሕግ አስከባሪ አካላት ሰብዓዊ መብቶችን አክብረው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡

ኮሚሽኑ በምርጫ ሂደት የሰብዓዊ መብት ጥበቃን አስመልክቶ ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር ምክክር አካሂዷል።

መድረኩ የሕግ አስከባሪ አካላት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበር፣ የማስከበር እና የማሟላት ኃላፊነት አኳያ፣ በቅድመ ምርጫው፣ በምርጫው ዕለትና በድኅረ-ምርጫው ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ የሕግ አስከባሪ አካላትን ግዴታና ኃላፊነቶች ለማስታወስ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በተለይም ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የመዘዋወር፣ የመሰብሰብ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶችን ጨምሮ ሌሎች በምርጫ ወቅት ትኩረት የሚሹ ሰብዓዊ መብቶችን በማረጋገጥ ረገድ የሕግ አስከባሪ አካላት ሚና በዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የሕግ አስከባሪ ተቋማት ባልደረቦችም ተግባራቸውን ሰብዓዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ ለማከናወን ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለፃቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላታል፡፡

ኮሚሽኑ በምርጫው ወቅት የሕግ አስከባሪ አካላት በገለልተኝነት ተግባራቸውን በመወጣት የዜጎች መብቶችን እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ እንዲሁም ጥሰቶች ሲኖሩ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ አጽንኦት ሰጥቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.