Fana: At a Speed of Life!

በምርጫ ወቅት ከሳይበር ደህንነት አንፃር ማህበረሰቡ እንዲሁም ተቋማት ሊያስተውሏቸው የሚገቡ ጉዳዩች ምንድናቸው?

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መጪው ሀገራዊ ምርጫን ተከትሎ መሰረት የሌላቸውና ሆን ተብሎ ህብረተሱቡን ለማደናገር የሚወጡ ሀሰተኛ መረጃዎች በስፋት ሊሰራጩ ይችላሉ፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሀገራዊ ምርጫውን ተከትሎ የሃገሪቱ ወሳኝ መሰረተ ልማቶችና ተቋማት ለሳይበር ጥቃት ሰለባ ሊሆኑ ይችላሉ ነው ያለው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፡፡
ለዚህም በተቋማት በኩል በጥቂቱ መወሰድ የሚገባቸው የጥንቃቄ ዕርምጃዎች ተቋማት የማይጠቀሙባቸው ድረ-ገጾቻቸውን፣ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እንዲሁም የተለያዩ የሳይበር ሀብቶቻቸውን ከአገልግሎት ውጪ እንዲያደርጉ፤ ከዚህ ቀደም የምንጠቀምባቸውን የይለፍ ቃል በአዲስ እና ጠንካራ የይለፍ ቃል መቀየር ይገኝበታል፡፡
እንዲሁም ከኮምፒውተር ስርዓት ጋር የተገኛኙ መገልገያዎች እንደ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ታብሌቶች እና የመሳሰሉት እንዳይሰረቁ፣ አንዳይጠፉ ወይም ጉዳዩ የማይመለከተው አካል እንዳይጠቀምበት አካለዊ ደህንነቱን ማረጋገጥ፤ የግል በሆኑ መገልገያዎቻች ላይ የተቋማትን ቁልፍ መረጃዎች አለመለዋወጥ አንዲሁም በተቋማት መገልገያዎች የግል የሆኑ ጉዳዩችን አለማስተናገድ ይገባል ፡፡
በተጨማሪም በማህበራዊ ሚዲያ ተደራሽ የሚደረጉ ይዘቶችን የሚያስተዳድር ኃላፊ መመደብ፤ የድረ-ገጹን ባካፕ በየጊዜው ይውሰዱ ምን አልባት የመረጃ ጥቃት ሙከራ ቢደርግ ጉዳቱን ለመቀነስ መጥባበቂያ መረጃ ሆኖ ስለሚያገለግል፤ በኮምፒዉተር ስርዓቶቻችን ያልተለመዱ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ ለተቋሞቻቸው የበላይ አካል ማሳወቅ ይገባል ተብሏል፡፡
ያልተለመዱ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩም በነጻ ስልክ መስመር 933 በመጠቀም ማሳወቅ እንደሚገባ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.