Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ከ110 በላይ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምስራቅ ሃረርጌ ዞን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶችን መያዙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ኃላፊ ኮማንደር ናስር መሀመድ  እንደገለጹት የጦር መሳሪያዎቹ የተያዙት በዞኑ 20 ወረዳዎች በተደረገው ፍተሻ ነው።

ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገው ፍተሻ 103 ሽጉጥ፣ 7 ክላሽንኮቭ ፣25 የተለያዩ ቦንቦች፣ ከ5 ሺህ በላይ የሽጉጥ፣ የክላሽንኮቭ፣ የተለያዩ ጥይቶችና የጥይት ካርታዎች መያዛቸውን ተናግረዋል።

እንዲሁም ቪንቶቭ ፣ኤስኬ ኤስና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ የተለያየዩ የሬዲዮ መገናኛዎችም እንደተያዙ ገልፀዋል።

በዚህም 66 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው 24ቱ በፍርድ ቤት የክስ መዝገብ የተከፈተባቸው ሲሆን 40ዎቹ ላይ ማስረጃ እየተሰበሰበ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሌሎች 56 ግለሰቦች ደግሞ ከኦነግ ሸኔና ከጁንታው ህወሃት ቡድን ጋር አብረው እንደሚሰሩ መረጃ ተገኝቶባቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር ናስር መሀመድ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.