Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጭናክሰን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ አስታወቀ፡፡
አደጋው ዛሬ ከቀኑ 5 ሰዓት አካባቢ ከቆቦ ቀበሌ ወደ ጭናክሰን ከተማ 29 ሰዎችንና እህል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ ተሽከርካሪ በመገልበጡ የደረሰ ነው፡፡
በዚህም የአምስት ሰዎች ህይወት ወዲያኑ ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ኃላፊ ኮማደር አህመዲን መሐመድ ገልፀዋል፡፡
በአደጋው ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች በተጨማሪ በሶስት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ፣በ14 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም ለተጨማሪ ህክምና ወደ ሀረር መላካቸውን የገለጹት ኮማንደር አህመዲን የአደጋው መንስኤ ከልክ በላይ ፍጥነት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሽከርካሪውም አደጋው ከደረሰ በኋላ ከአካባቢው በመሰወሩ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተሾመ ኃይሉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.