Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የኮትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት የተከማቸ ግምታዊ ዋጋቸው በአንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ኢኒስፔስተር ቶሎሳ ጐሹ በተለይም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ ከህብረተሰብ በደረሰ ጥቆማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በህገ ወጥ መንገድ ተከማችተው የተገኙ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ፣ የዝናብ ሸራ ላስቲክና የተለያዩ ዓይነት የሲጋራ አይነቶች መያዛቸውን ነው የገለጹት።

እነዚህ የተያዙት ህገ ወጥ የኮትሮባንድ እቃዎች ዋጋቸው አንድ ሚሊየን ዘጠኝ መቶ አስራ አንድ ሺህ ሰባት መቶ አስራ አራት ብር የሚያወጡ መሆናቸውን የጠቆሙት ኢንስፔስተር ቶሎሳ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በተደጋጋሚ ጊዜያት ህገ ወጥ የኮትሮባንድ እቃዎች እየተያዙ በመሆኑ አሁንም ህብረተሰብ ጥቆማውን አጠናክሮ ለፖሊስ እንዲያሳውቅ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.