Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ጎጃም ዞን እናርጅ እናውጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፤ ነሀሴ 22 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን እናርጅ እናውጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ።

አደጋው የደረሰው ከደብረ ወርቅ ከተማ ወደ መጣያ ደጅ አጋምና ቀበሌ የሚጓዝ ባጃጅ ከደብረ ታቦር ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ ሃገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡

የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ስማቸው አደጋው ከረፋዱ 5 ሰዓት አካባቢ ደጅ አጋምና ቀበሌ ኪዳነ ምህረት ልዩ ቦታው ከሻም ወንዝ አካባቢ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በአደጋው የባጃጅ ሾፌሩን ጨምሮ የሶስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ ሁለቱ ሰዎች ባልና ሚስት መሆናቸውን ኮማንደር ስማቸው ገልጸዋል።

ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ሴት በደብረ ወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል ብለዋል።

ኮማንደር ስማቸው የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በሰላም አሰፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.