Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ሸዋ ዞን ለጥፋት ተልዕኮ የተዘጋጀ የተለያየ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በምዕራብ ሸዋ ዞን አስር ወረዳዎች ለጥፋት ተልዕኮ የተዘጋጀ የተለያየ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደንብ ልብስ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።
ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 35 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራና ፍትህ አሰጣጥ ሀላፊ ኮማንደር ኑረሳ አካና ÷የጦር መሳሪያዎቹ የተገኙት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ሰሞኑን በወረዳዎቹ የተለያዩ ቤቶች በተደረገ ፍተሻ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም በቁጥጥር ስር ከዋሉት የጦር መሳሪያዎች መካከል ዘጠኝ ሽጉጥ፣ አራት ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 16 ቦምብ፣ ሁለት ፈንጂዎች፣ ከአምስት ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶችና አስር ገጀራዎች እንዲሁም 22 የቀድሞ የኦሮሚያ ፖሊስ እና ሌሎች የደንብ ልብሶች መያዛቸውን አስረድተዋል።
ሃላፊው ህብረተሰቡ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለጸጥታ አካላት በመጠቆም፣ለመከላከልናየአካባቢውን ሰላም ነቅቶ በመጠበቅና ወንጀልን በጋራ ለመከላከል ላደረገው ትብብር ምስጋና አቅርበው አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.