Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ሸዋ ዞን 21 የሸኔ አባላት በሰላም ለመንግስት እጃቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014( ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወረዳ 21 የሽብር ቡድኑ ሸኔ አባላት በሰላም ለመንግስት እጃቸውን ሰጥተዋል።
አባላቱ የሽብር ቡድኑ ሸኔ ሀገርን ለማፍረስ እየፈጸመ ያለውን ጥቃት በመቃወም ነው በሰላም እጃቸውን ለመንግስት የሰጡት።
የኦሮሞ ህዝብ አሸባሪው ሸኔ በንጹሃን ዜጎች እና ንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን መገንዘብ እንዳለበትም ጠቁመዋል አባላቱ።
እጃቸውን ከሰጡ የሽብር ቡድኑ አባላት ጋር የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች እና ገንዘቦች መያዛቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.