Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ አርሲ ኤበን አርሲ ወረዳ ሦስት መኪና ጭነት ካናቢስ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ኤበን አርሲ ወረዳ ቡኮ ዎልዳ ቀበሌ ሦስት መኪና ጭነት ካናቢስ የተሰኘው አደንዛዥ እጽ መያዙን የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዳኙ ዋሪቱ አስታወቁ።
አደንዛዥ እጹ ሊያዝ የቻለው በበርካታ አርሶ አደሮች ማሳ ላይ በተደረገ ድንገተኛ አሰሳ እና የህብረተሰቡ ጥቆማ መሆኑ ተገልጿል።
እንዲህ አይነት ድርጊት በወረዳው ያልተለመደ እና አዲስ ነው ያሉት ምክትል አስተዳዳሪው፥ ደርጊቱ የተሳተፉ አካላት ከዚህ መሰል ተግባር እንዲቆጠቡ እና ህብረተሰቡ የሚደረገው ጥቆማ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በ11 የአርሶ አደር ማሳ ውስጥ የተገኘው ከ 1 ነጥብ 5 ሄክታር ላይ የተሰበሰበ ሦስት መኪና ጭነት ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።
በሌሎች ሦስት ቀብሌዎች ውስጥ ጥርጣሬዎች እንዳሉም የኤበን አርሲ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ክብሬ ገመዲ ገልጸዋል።
እስካሁን በተደረገ ኦፕሬሽን 4 ተጠርጣሪ ግለሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፥ ሌሎች ተጠርጣሪዎችንም ለመያዝ ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ዋና ሳጅን አቡ ተሺቴ ተናግረዋል።
ምንጭ:- የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
53
Engagements
Boost Post
46
3 Comments
4 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.