Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ጉጂ ዞን የሠላም አማራጭ የተቀበሉ 436 የኦነግ ሸኔ አባላት ከህዝብ ጋር እንዲቀላቀሉ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 05፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላት የነበሩና የሠላም አማራጭ የተቀበሉ 436 ግለሰቦች ሥልጠና በመወስድ ከህዝብ ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጉን የምዕራብ ጉጂ ዞን ጸጥታና አስተዳደር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ደስታ ኢታና እንዳሉት የዞኑ ህዝብ የጥፋት ቡድኑን አባላት አሳልፎ በመስጠቱ የምዕራብ ጉጂ ዞን ወደ ቀደመ ሠላማዊ እንቅስቃሴው ተመልሷል፡፡

የጥፋት ተልዕኮ በመቀበል ሲንቀሳቀሱ የነበረና የቀረበላቸውን የሠላም አማራጭ የተቀበሉ 436 የኦነግ ሸኔ አባላት በዞኑ ህዝብና በጸጥታ ሀይሉ የጋራ ጥምረት በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ አስረድተዋል፡፡

በይቅርታ ታልፈው በህግ የበላይነትና ሥነ ልቦና ዝግጅት ዙሪያ ሥልጠና ወስደው ከህዝቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ምክርና ተግሳጽ ተቀብለው ወደ ሠላማዊ ህይወት ለመመለስ ፈቃደኛ ባልሆኑት ላይ እርምጃ መወሰዱንና 350 የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የዞኑን መልካም ገጽታ ለማጠልሸት ሠላም እንደሌለ ተደርጎ የሚናፈሰው አሉባልታ ፍጹም ሀሰትና ከእውነት የራቀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ከአባላቱ መካከል ገላ ዋቆ እና ፊሮምሳ ዋቆ በሚል በሁለት ስሞች የሚጠቀመው በሰጠው አስተያየት ኦነግ ሸኔ ከጥፋት በቀር ዓላማና ግብ የሌለውና ለህዝብ የማይጨነቅ በመሆኑ እራሱን ከቡድኑ ማግለሉን ተናግሯል፡፡

ሌላው የቡድኑ አባል ሞሮማ አሬሪ እና ኢማና ወባ በሚል ስሞች ይጠቀም የነበረው በበኩሉ ዓላማ ከሌለው የጥፋት ቡድኑ ጋር በመሆን ጊዜ ከማጥፋት ወደ ሠላም ተመልሶ የበደለውን ህዝብ ለመካስ እጅ መስጠቱን ተናግሯል፡፡

ህዝብና መንግስት ይቅር ባይ በመሆኑ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የጥፋት ተልዕኮ ለመፈጸም በጫካ ያሉም ወደ ሠላም እንዲመለሱ መልዕክቱን ማስተላለፉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.