Fana: At a Speed of Life!

በሞናኮ ዳይመንድ ሊግ አትሌት ወርቅውኃ ጌታቸው አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሌሊት ላይ በሞናኮ በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ የ3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ውድድር አትሌት ወርቅውኃ ጌታቸው አሸነፈች፡፡
በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር አትሌት ወርቅውኃ ጌታቸው 9 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ ከ19 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት አንደኛ ስትወጣ÷ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ደግሞ 9 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ሆና ጨርሳለች፡፡
በሌላ መርሐ ግብር በወንዶች 3 ሺህ ሜትር÷ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 7 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ ከ81 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ጥላሁን ኃይሌ 7 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ 24 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ ሰባተኛ ደረጃን ይዘ አጠናቀዋል፡፡
እንዲሁም በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ደግሞ አትሌት ሂሩት መሸሻ 4 ደቂቃ ከ51 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ አራተኛ ሆና ማጠናቀቋን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.