Fana: At a Speed of Life!

በሞጆ ከተማ የእሳት አደጋ ደረሠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሞጆ ከተማ ” ገበያ ” ተብሎ በሚጠራዉ ስፍራ ዛሬ ለሊት 10፡00 ላይ የእሳት አደጋ መድርሱ ተሰምቷል፡

በደረሰው የእሳት አደጋም 60 የሚሆኑ ሱቆች መውደማቸውን የከተማው የመንግስት ኩሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የእሳት አደጋው ወደሌሎች አካባቢ እንዳይዛመት በህብረተሰቡና በእሳት አደጋ ሰራተኞች ትብብር በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉ ተገልጿል፡፡

አደጋውን ለመከላከልም የእሳት አደጋ ተሸከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ፣ ከአዳማ፣ ከቢሾፍቱ እና ከግል ድርጅቶች የተጣጥተው ወደ ቦታው መምጣታቸውም ተነግሯል፡፡

በእሳት አደጋውም የወደመውን የንብረት መጠን ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ መሆኑን ሞጆ የሞጆ ከተማ ፖሊስ መመሪያ ሃላፊ ኮማንደር ሙሃመድ አህመድ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.