Fana: At a Speed of Life!

ታንዛኒያዊውፕሮፌሰር አብዱልራዛቅ ጉርናህ የ2021 የኖቤል ተሸላሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ታንዛኒያዊው ደራሲ ፕሮፌሰር አብዱልራዛቅ ጉርናህ የ2021 የሥነ-ፅሁፍ ዘርፍ ተሸላሚ መሆናቸው ተሰማ፡፡

ተሸላሚ መሆናቸውን ያስታወቀው የስዊድን አካዳሚ ሲሆን መረጃዎች እንደሚያመላክቱት አሸናፊ ያደረጋቸው ሥነ-ፅሁፍም በቅኝ ግዛት አስከፊነት እና በባሕልና አህጉራት ውስጥ ያለውን የስደተኞች እጣ ፋንታ የሚተርከው መጽሐፋቸው እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

አብዱልራዛቅ ጉርናህ በፈረንጆቹ 1948 ተወልደው ያደጉት በዛንዚባር ሕንድ ውቅያኖስ አቅራቢያ ሲሆን በፈረንጆቹ 1960 በስደት ወደ እንግሊዝ ማምራታቸው ነው የተመላከተው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ደራሲው በእንግሊዝ ኬንት ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ሲሆኑ በፈረንጆቹ 1994 “ፓራዳይዝ” የተባለው መጽሐፋቸው ለአሸናፊነት ባያበቃቸውም ለውድድር ቀርቦ ነበር ተብሏል፡፡

በሽልማቱ ደራሲው የወርቅ ሜዳሊያ እና 1 ነጥብ 14 ሚሊየን ዶላር እንዳገኙም ተገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው የሥነ-ጽሁፍ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት÷ ኧርነስት ሄሚንግ ዌይ፣ገብሪኤል ጋርሺያ ማርኩዌዝ እና ቶኒ ሞሪሰን፣ ፓብሎ ኔሩዳ፣ ጆሴፍ ብሮድስኪ፣ ራቢንድርናት ታጎር፣ሃሮልድ ፒንተር፣ ኢዩጊን ኦኔል አሸናፊዎች እንደነበሩ ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡

በዓለማየሁ ገረመው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.