Fana: At a Speed of Life!

በሮቢት ከተማ የብልፅግና ፓርቲን እና የለውጥ አመራሩን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ ሮቢት ከተማ የብልፅግና ፓርቲን እና የለውጥ አመራሩን የሚደግፍ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ ፡፡
በድጋፍ ሰልፉ ለውጡን የሚያደናቅፍ የሴራ ፖለቲካን እናወግዛለን፣ ፈተናዎችን እየመከትን የለውጡን ዘላቂነት እናረጋግጣለን፣ ጽንፈኝነት የሰላምና የአብሮነት እሴት ፀር ነው፣ በጁንታው መቃብር ላይ ብልፅግና፣ የህዝቦች አንድነት ይለመልማል፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጁንታውን ቡድን ለማምከን የሰጡትን በሳል አመራር እናደንቃለን፣ ጁንታውን የማፍረስ ድል የጋራ ጥረታችን ውጤት ነው የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን ማሰማታቸውን ከራያ ቆቦ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.