Fana: At a Speed of Life!

በሮዝ ቀለም ፍቅር የተጠመደችው ወጣት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስዊዘርላንዳዊቷ ወጣት ለሮዝ ቀለም ባላት የበዛ ፍቅር ከሰሞኑ መነጋገሪያ ሆናለች።

ወጣቷ የስዊዘርላድ ዜግነት ያላት እና መምህር እንደሆነች ተነግሯል።

የ32 ዓመት እድሜ ያላት ወጣቷ በእጅጉ የሮዝ ቀለም ወዳጅ ስትሆን ከ15 ዓመት በላይ የሮዝ ቀለም ያለው አልባሳትን ብቻ ስትለብስ ቆይታለች።

ከአልባሳቷ ባሻገርም አሁን ላይ የምትኖርበት አፓርታማ ሳይቀር በሮዝ ቀለም ያጌጠ ነው።

በልጅነቷ እንደማንኛውም ልጅ ሮዝ ቀለም ያለው ልብስ እንደምትለብስ የምተናገረው ወጣቷ ከ16 ዓመትዋ በኋላ ግን የተለየ ፍቅር እንዳደረባት እና የሮዝ ቀለም ያለው አልባሳት ብቻ መልበስ እንደጀመረች ገልፃለች፡፡

ወጣቷ ለሰርግ ስነ ስርዓቷም ቢሆን ከሮዝ የሙሽራ ቀሚስ በስተቀር እንደማትለብስ አስታውቃለች።

በዚህም ከምታስተምርበት ትምህርት ቤትም ሆነ ከቤተሰቦቿ ቅሬታ አልቀረበባትም የተባለ ሲሆን፥ እሷም ሮዝ እንድትለብስ የማይፈቅድላትን ሥራ በጭራሽ እንደማትቀበል ተናግራለች።

የምታስተምርበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችም “ሚስ ሮዝ” ይሏታል ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ኦዲቲሴንተራል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.