Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የተከሰተ የአንበጣ መንጋ 12 ሺህ ሄክታር የደረሰ ሰብል አወደመ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ተከስቶ በሰብል ከተሸፈነው 48 ሺህ 700 ሄክታር መሬት ውስጥ 12 ሺህ ሄክታር የደረሰ ሰብልን ማውደሙ ተገለፀ፡፡
መንጋው በወረዳው 27 ቀበሌዎች በሰብል ከለማው 48 ሺህ 700 ሄክታር መሬት ውስጥ በ13 ቀበሌዎች ተከስቶ 12 ሺህ ሄክታር የደረሰ ሰብልን ነው ያወደመው፡፡
በዚህም በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የጤፍ ሰብል 95 በመቶ በአንበጣ መንጋ መውደሙ ታውቋል፡፡
ወረርሽኙ ከመስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መታየት ቢጀምርም ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የጀመረው ግን ከጥቅምት 5 ቀን ጀምሮ ነው ተብሏል፡፡
የአንበጣ መንጋው አሁንም በወረዳው ቆላማ ቀበሌዎች ተንሰራፍቶ ቢገኝም በወረዳው ወጣቶች ባህላዊ የመከላከል ዘዴ፣ በፌደራል በኩል በአውሮፕላን ርጭት፣ ከሰሜን ሸዋ ዞን በተወጣጡ በጎ ፍቃደኞች አንበጣው የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው፡፡
በፀጋዬ ንጉስ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.