Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 13፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሕደቡ አቦቴ እና በወረጃርሶ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል፡፡
በመከላከያ ሰራዊት የጥምር ፀጥታ አካላት አስተባበሪ እና በኮማንዶ ክፍለ ጦር የሬጅመንት ዋና አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ታሄል ሬድ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በተደረገው ሁሉን አቀፍ ዘመቻ በርካታ አመርቂ ድሎች እየተመዘገቡ ይገኛል ብለዋል።
በዞኑ ቀጣይነት ያለው ሰላም ለማስፈን በአካባቢው የተሰማሩት የጥምር ፀጥታ አካላት በሽብር ቡድኑ ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
እንደ ዋና አዛዡ ገለፃ እስከ አሁን በተደረጉ ዘመቻዎች 44 የቡድኑ አባላት እርምጃ ሲወሰድባቸው 5 አባላት ተማርከዋል፡፡
በዘመቻው 18 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች የተማረኩ ሲሆን የሽብር ቡድኑ ሲጠቀምበት የነበረ 19 ኩንታል እህል መያዙን እና 233 የቡድኑ አባላት በሰላም እጅ መስጠታቸውን ተናግረዋል።
የወረጃርሶ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ አየለ መንግስቱ በበኩላቸው ከአካባቢው ህብረተሰብ፣ ከአገር ሽማግሌዎችና ከአባገዳዎች ጋር በመሆን በተሰራው የተቀናጀ ትብብር የተገኘው ድል አበረታች መሆኑን ጠቁመዋል።
አሁን ላይም ወረዳው ሰላም ማስፈን መቻሉን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.