Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ዕዝ ላይ በተፈፀመው ጥቃት የተጎዱ የሠራዊቱ አባላት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር አመራር አባላት በሰሜን ዕዝ ላይ በተፈፀመው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአዲስ አበባ የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ተገኝተው ጎብኝተዋል።

ሚኒስቴሩ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታሉ ለሚገኙ የሠራዊቱ አባላት የገና በዓል ስጦታ አበርክቶላቸዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ ሕይወት ሃይሉ በጉብኝታቸው ጉዳት የደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ማየት እንደቻሉ ገልጸዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከጉብኝት ባለፈ የስነ-ልቦና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንና ሴት ጀግኖችንም በተለያየ መንገድ እንደሚያበረታታ ተናግረዋል።

የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል እየሰጠ ያለው አገልግሎትና ለሠራዊቱ አባላት እያደረገላቸው ያለው የሕክምና ክትትል መልካም እንደሆነም ገልፀዋል።

ሚኒስቴሩ ሴት የሠራዊቱን አባላት በቋሚነት ለመደገፍ ከተለያዩ አካላት ጋር እየመከረ እንደሆነም መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመከላከያ ሚኒስቴር የሴቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ ድጋፉ ለሠራዊቱ አባላት የሞራል ስንቅ የሚሆንና ለበለጠ ግዳጅ የሚያነሳሳ እንደሚሆን ተናግረዋል።

‘ከጎናችሁ ነን’ በማለት እየተደረገ ያለው ድጋፍ ሠራዊቱን ለበለጠ መስዋዕትነት የሚያነሳሳ መሆኑን ነው የገለጹት።

በሆስፒታሉ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላት እየተሰጠ ያለው የሕክምና አገልግሎት ጥሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

ሚኒስቴሩ ከጉብኝቱ በኋላ የአልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ስጦታ ለሠራዊቱ አባላት አበርክቷል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.