Fana: At a Speed of Life!

በሰቆጣ ከተማ ቦምብ፣ ሽጉጥ እና ተተኳሽ ጥይቶች የተገኘበት ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰቆጣ ከተማ ቦምብ፣ ሽጉጥ እና ተተኳሽ ጥይቶችን በህገ ወጥ መንገድ ይዞ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ተወካይ ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር አበራ አግኝቸው ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹን በአገልግል ውስጥ ሸሽጎ በአውቶቡስ ወደ ባህር ዳር ለማጓጓዝ ሲሞክር ነው ብለዋል።

ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በሰቆጣ ከተማ መናኸሪያ ትናንት ከንጋቱ 11 ሰዓት አካባቢ በተደረገው ፍተሻ ግለሰቡ የሸሸጋቸው 14 “ኤፍ ዋን ” ቦምብ፣ አንድ ሽጉጥ፣  152  የክላሽንኮቭ እና 32 የቃታ ተተኳሽ ጥይቶች ማግኘታቸውን አመልክተዋል።

በህግ ቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ የሚደረግበት ተጨማሪ ምርመራ ሲጠናቀቅ ለፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ረዳት ኢንስፔክተር አበራ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.