Fana: At a Speed of Life!

በሰባት የአፍሪካ ሃገራት የሰውነት የኮሮና ቫይረስ የመከላከል አቅም ምርመራ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰባት የአፍሪካ ሃገራት የሰውነት የኮሮና ቫይረስ የመከላከል አቅም ምርመራ ሊጀመር መሆኑ ተነገረ፡፡

የሰውነት የመከላከል አቅም ምርመራው በቀጣዩ ሳምንት እንደሚካሄድ የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል አስታውቋል፡፡

ምርመራው ቫይረሱ በአህጉሪቱ ያለውን ስርጭት ለማወቅ እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡

ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ፣ ካሜሮን፣ ናይጄሪያ እና ሞሮኮ ምርመራው የሚካሄድባቸው ሃገራት ናቸው ተብሏል፡፡

በአህጉሪቱ 10 ሚሊየን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማካሄድ ታቅዶ እስካሁን 9 ነጥብ 4 ሚሊየን ምርመራ ማድረግ ተችሏል፡፡

የማዕከሉ ሃላፊ ጆን ኬንካሶንግ አፍሪካ ክትባት ለማግኘት እየሄደችበት ያለው መንገድ መሻሻል የታየበት ነው ብለዋል፡፡

እንደ ጆንሆፕኪንስ መረጃ እስካሁን በአህጉሪቱ 1 ሚሊየን 84 ሺህ 904 ሰወች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.