Fana: At a Speed of Life!

በሱዳን አንድ ግድብ ተደርምሶ 600 ቤቶች ወደሙ

አዲስ አበባ ፣ ሐሌ 25 ፡ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት የሚገኝ አንድ ግድብ ተደርምሶ 600 ቤቶችን ማውደሙ ተገለፀ።

የሱዳን መገናኛ ብዙሃንን ዋቢ አድርጎ ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው ቦት የተባለው ይህ ግድብ 6 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃን የያዘ ነበር።

ድንገት በግድቡ ላይ የመደርመስ አደጋ መድረሱን ተከትሎ በሶስት አቅጣጫ ጎርፍ የተፈጠረ ሲሆን፥ በአቅራቢያ የምትገኝ ቦት ከተማን አጥለቅልቋል።

የአካባቢው ባለስልጣናት የግድብ መደርመሱ የበርካታ ሰዎችን መፈናቀል ሊያስከትል እና የማህብራዊ አገልግሎቶችን ሊያስተጓጉል እንደሚችል ነው ያስጠነቀቁት።

በሱዳን ሰኔ እና ሀምሌ ወራት በሚኖር ከፍተኛ ዝናብ የጎርፍ መጥለቅለቆች የተለመዱ ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.