Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል የ81 ህገ ወጥ የመንግስት ሰራተኞች ቅጥርና የደረጃ እድገት ተሰረዘ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የ81 ህገ ወጥ የመንግስት ሰራተኞች ቅጥርና የ12 ህገ ወጥ የደረጃ እድገት እንዲሰረዝ መደረጉን የክልሉ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ገለጸ።

ኮሚሽኑ የመንግስትና የህዝብ ንብረት የሆነ 7 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ከምዝበራ ማዳኑንም ገልጿል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ስጦታው ወንጫኖ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለኮሚሽኑ ከቀረቡለት 56 አስቸኳይ የሙስና መከላከል ጥያዎች ውስጥ 54ቱን ተቀብሎ ምላሽ ሰጥቷል።

“በዚህም የ81 ሰዎች ህገ ወጥ የመንግስት ሰራተኛ ቅጥርና የ12 ሰዎች ህገ ወጥ የደረጃ እድገት እንዲሰረዝ ተደርጓል” ብለዋል።
ከሁለት ቦታ ደመወዝ ሲበሉ የነበሩና ሌሎችም የመንግስት ሰራተኞች በህግ እንዲጠየቁ ሰነድ በማደራጀት ለሚመለከተው የህግ አካል መተላለፉን ተናግረዋል።

በሀሰት ለተደራጁ ዘጠኝ የአረንጓዴ ፓርክ ልማትና ኮብል ስቶን ማህበራት ክፍያ ሊፈጸም የነበረውን ጨምሮ 2 ሚሊየን 367 ሺህ ብር በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ስራ ማዳን መቻሉን ጠቁመዋል።

ከተለያዩ ተቋማት ተመዝብሮ የነበረ 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በኦዲት ግኝት ተረጋግጦ ተመላሽ እንዲደረግ ኮሚሽኑ መስራቱን አስረድተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.