Fana: At a Speed of Life!

በሳምባ ኢንፌክሽን ዛሬ ማለዳ ህይወታቸው ያለፈው የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ የኮሮና ቫይረስ እንዳልነበረባቸው በምርመራ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምባ ኢንፌክሽን ዛሬ ማለዳ ህይወታቸው ያለፈው የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ የኮሮናቫይረስ እንዳልነበረባቸው በላብራቶሪ በምርመራ መረጋገጡን ነው የጤና ሚኒስቴር የገለጸው።

የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ተገኔ ረጋሳ እንደተናገሩት ግለሰቡ የሳምባ ኢንፌክሽን እንዳለባቸው ቢታወቅም የኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ስለመሆን አለመሆናቸው ለማረጋገጥ ናሙናቸው ተወስዶ ምርመራ ተደርጎበታል።

በዚሁ መሰረት ግለሰቡ ከኮሮና ቫይረስ ነጻ እንደሆኑ ተረጋግጧል ነው ያሉት።

ግለሰቡ በለይቶ ማቆያ የነበሩና የሳምባ ኢንፌክሽን ህመም ምልክቶች ጋር በተያያዘ ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ዛሬ ህይወታቸው ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ዛሬ ረፋድ ላይ መግለጻቸውን ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.