Fana: At a Speed of Life!

በሳዑዲ ዓረቢያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕከተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሌንጮ ባቲ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) – በሳዑዲ ዓረቢያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ሌንጮ ባቲ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ በሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የፕሮቶኮል ጉዳዮች ኃላፊ ለመሻሪ ቢን ነሂት አቅርበዋል፡፡

አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ባቀረቡበት ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል ስላለው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት በተለይም በሳዑዲ ዓረቢያ ስለሚኖሩት ኢትዮጵያዊያንን በተመለከተ ያለውን ትብብር በሚጠናከርበት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

አምባሳደር ሌንጮ ባቲ የትግራይ ክልል ስለተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻና የሰላም መልሶ ግንባታ ሂደት፣ በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም በሱዳንና ኢትዮጵያ መካከል ስለተከሰተው የድንበር ውዝግብና ታላቁን የሕዳሴ ግድብ በተመለከተ ለፕሮቶኮል ጉዳዮች ኃላፊ ለመሻሪ ቢን ነሂት አብራርተውላቸዋል።

በውይይታቸው በኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል በፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች እንዲሁም ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትብብሮችን ለማጠናከር በጋራ ለመስራት ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.