Fana: At a Speed of Life!

በስልጤ ዞን ለሚገነባው የካሊድ ዲጆ የግድብና መስኖ ፕሮጀክት በነገው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ይቀመጣል

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ በስልጤ ዞን ለሚገነባው የካሊድ ዲጆ የግድብና መስኖ ፕሮጀክት በነገው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ይቀመጣል።

ግድቡ 1 ሺህ 731 ሜትር ርዝመትና ከ30 በላይ ሜትር ከፍታ ሲኖረው ፕሮጀክቱ ከ1 ሺህ 800 ሄክታር በላይ መሬት የማልማት አቅም እንደሚኖረው ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ ከ3 ሺህ 600 በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ይጠበቃል።

በስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳና ወራቤ ከተማ አስተዳደር በሚገኙት ካሊድና ዲጆ ወንዞች ላይ የሚገነባው ፕሮጀክቱ ነገ ጥር 2 2013 የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦ ስራ የሚጀምር ሲሆን በመርሃግብሩ የፌደራልና የደቡብ ክልል የስራ ኃላፊዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

 

በአፈወርቅ እያዩ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.