Fana: At a Speed of Life!

በስልጤ ዞን የሚከበረው 113ኛው የአልከሶ መውሊድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በስልጤ ዞን ዘንድሮ የሚከበረው 113ኛው የአልከሶ መውሊድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ተገለጸ።

የዞኑ አስተዳደር መውሊዱን አስመልክቶ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በወራቤ ከተማ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ተደርሷል።

ልክ እንደወትሮው ሁሉ ዘንድሮ ለ113ኛ ጊዜ ሊከበር ሳምንት የቀረው የአልከሶ መውሊድ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ከፊት ለፊቱ ተደቅኗል።

በዞኑ ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተጋላጭነት በር ይከፍታሉ ተብለው ከተለዩ ስጋቶች መካከል መውሊድ አንዱ ነው።

በዚሁ መነሻ የወረርሽኙን ተጋላጭነት ለመቀነስ የስልጤ ዞን አስተዳዳር ከሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎችና ተወካዮች ጋር በሰፊው መክሯል።

በዞኑ በሀይማኖታዊና በባህላዊ ክንዋኔዎች የሚከበረው የአልከሶ መውሊድን ለማክበር የዞኑ አስተዳደር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

ይሁን እንጅ አሁን ላይ በዓለም ላይ ብሎም በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ስጋት በመደቀኑ መውሊዱን ከሚመለከታቸው ጋር ተወያይቶ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.