Fana: At a Speed of Life!

በስፔን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በስፔን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎቸ ቁጥር ከአንድ ሚሊየን ማለፉ ተነገረ፡፡
 
ስፔን በአውሮፓ ከፍተኛ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከተመዘገበባቸው ሃገራት የመጀመሪያዋ ሆናለች ነው የተባለው፡፡
 
ትናንት በቫይረሱ የተያዙትን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት 1 ሚሊየን 5 ሺህ 295 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡
 
ይህንንም ተከትሎም ከ1 ሚሊየን በላይ ዜጎቻቸው በቫይረሱ ከተያዙባቸው የዓለም ሃገራት መካከል ስፔን ስድስተኛዋ መሆኗ ነው የተሰማው፡፡
 
እስካሁን አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና አርጀንቲና ከ1 ሚሊየን በላይ ዜጎቻቸው በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡
 
በጣልያን በአንድ ቀን 15 ሺህ 199 ሰዎች መያዛቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ወረርሽኙ ዳግም ከተከሰተ በኋላ በአንድ ቀን የተመዘገበ ትልቅ ቁጥር ነው ተብሏል፡፡
 
በሌሎች የአውሮፓ ሃገራትም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
 
በዚህ ሳቢያም ሃገራቱ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተለያዩ ክልከላዎችን እያወጁ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
 
ምንጭ፡-ቢቢሲ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.