Fana: At a Speed of Life!

በስፔን የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከሰተ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን የጣለው ከባድ ዝናብ የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከተለ።

ጎርፉ በተለይም በሰሜን ምስራቅ የካታሎኒያ ግዛት የሚገኙ ከተሞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ከዚህ ባለፈም ከመዲናዋ ማድሪድ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ የመካከለኛው ስፔን ግዛቶችም በጎርፉ ሳቢያ መጎዳታቸውን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች የሃይል አቅርቦት የተቋረጠባቸው ሲሆን፥ ከተሞችን የሚያገናኙ አውራ ጎዳናዎችና የባቡር ሃዲዶችም ዝግ ሆነዋል ነው የተባለው።

በጎርፉ ሳቢያ በመሰረተ ልማት ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የበርካቶች ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረም ነው የተገለጸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.