Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የማሰራጨት ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች የተደረገውን ድጋፍ ወደ ህብረተሰቡ የማሰራጨት ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ በርካታ አርብቶ አደሮች ድጋፍ ይሻሉ ነው የተባለው፡፡

የተለያዩ ክልሎች በድርቁ ለተጎዱ ዜጎች በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ የክልሉ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ቢሮ ገልጿል።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ሳዲቅ አብዱልቃድር እንደተናገሩት ÷ በዛሬው እለት 20 ሺህ ኩንታል ምግብና ምግብ ነክ ድጋፍ ወደ ህብረተሰቡ የማሰራጨት ስራ ተጀምሯል፡፡

ይህም ዘይት፣ ሩዝ፣ ዱቄትና ሌሎች ሰብአዊ ድጋፎችን ያካተተ ሲሆን÷ ለ36 ወረዳዎች የሚዳረስና ለአንድ ወር የሚሆን ቀለብ መሆኑን ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ230 ሺህ በላይ እንስሳት ህይወት ሲያልፍ÷ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አርብቶ አደሮች ድጋፍ እንደሚሹ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በፈቲያ አብደላ እና በጌታሰው የሸዋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.