Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በአራት ወረዳዎች የጤና መድኅን አገልግሎት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በሚገኙ አራት ወረዳዎች የጤና መድኅን አገልግሎት የማስጀመር ሥነ ሥርዓት በአውበሬ ወረዳ ይፋ ተደርጓል።

የጤና መድኅን አገልግሎቱን ለማስጀመር በአውበሬ ወረዳ ስር የሚገኙ ነዋሪዎች ሦስት ሚሊየን ብር ማሰባሰባቸውንና የአገልግሎት ካርድ መውሰዳቸው ተገልጿል።

የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ዲኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ የጤና ሚኒስቴር በአውበሬ ወረዳ የተጀመረውን የጤና መድኅን ዋስትና ለማጠናከር እንደሚሠራ ጠቁመው የወረዳው ሕዝብም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ የጤና መድኅን ኤጄንሲ ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬሕይወት አበበ በበኩላቸው፥ የጤና መድኅን አገልግሎቱን በሶማሌ ክልል ለማዳረስ ኤጄንሲው እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡

የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ሓላፊ ዶክተር የሱፍ መሐመድ የክልሉ ጤና ቢሮ ለሕዝቡ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሁን የተጀመረው የጤና መድኅን አገልግሎት በአራርሶ፣ ኤረር እና ጎዴ ወረዳዎች እንደሚቀጥል መናገራቸውን የሶማሌ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.