Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ለሚበልጡ ሰዎች የኮሮና መከላከያ ክትባት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በሶማሌ ክልል ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ለሚበልጡ ሰዎች ሶስተኛው ዙር የኮሮና መከላከያ ክትባት መሰጠቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ ላለፉት 15 ቀናት የተካሄደው የክትባት መርሃ ግብር ከታቀደው ውስጥ በአብዛኛው መከናወኑን በቢሮው የእናቶች እና ሕፃናት ጤና ቡድን ተወካይ አቶ መሀመድ መሀሙድ ተናግረዋል ።

መከላከያ ክትባቱን ለ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰዎች ለመስጠት የተያዘው ግብ ለማሳካት በተጨማሪ ለ4 ቀናት እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

በክልሉ ሲሰጥ የቆየውና አሁንም የቀጠለው የክትባቱ መረሃ ግብር በክልሉ በሚገኙ ስድስት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ፣ የተለያዩ የጤና ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ 500 ጊዜያዊ ተንቀሳቃሽ ድንኳኖች መሆኑን ገልጸዋል።

በዕቅድ ከተያዘው ውስጥ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ ለሆኑ 1 ሚሊየን 415 ሺህ 457 ሰዎች መከተባቸውን አቶ መሀመድ መናገራቸውን ኢዜአ ።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.