Fana: At a Speed of Life!

በሶሪያ ኢድሊብ በተፈጸመ የአየር ጥቃት 18 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶሪያ ኢድሊብ ከተማ በተፈጸመ የአየር ጥቃት 18 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተነገረ።

ጥቃቱ በከተማዋ በሚገኝ የገበያ ስፍራ እና በኢንዱስትሪ ዞን ላይ የተፈጸመ ነው ተብሏል።

የአየር ጥቃቱ በወሩ መጀመሪያ ሩሲያ እና ቱርክ በአካባቢው የተኩስ አቁም ስምምነት ከደረሱ በኋላ የተፈጸመ ነው።

በስፍራው የሚንቀሳቀሰው ታዛቢ ቡድን የሩሲያ እና የሶሪያ መንግሥት አውሮፕላኖች ጥቃቱን መፈጸማቸውን ገልጿል።

ተፈጽሟል ስለተባለው የአየር ጥቃት ግን ሩሲያም ሆነች ሶሪያ ያሉት ነገር የለም።

ኢድሊብ በሶሪያ የአማጽያኑ የመጨረሻዋ ጠንካራ ይዞታ መሆኗ ይነገራል።

የሶሪያ መንግስትም ኢድሊብን ከአማጽያኑ በማስለቀቅ መልሶ ለመቆጣጠር ተደጋጋሚ ጥቃት እየፈጸመ ይገኛል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.