Fana: At a Speed of Life!

በሻምፒዮናው 3ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የጎዳና ላይ አቀባበል አየተደረገለት ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የጎዳና ላይ አቀባበል አየተደረገለት ነው፡፡

በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የልዑካን ቡድኑ፥ በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

ቡድኑ ዛሬ ከማለዳው 1 ሰዓት ከ30 ጀምሮ ከስካይ ላይት ሆቴል በመነሳት በአዲስ አበባ ከተማ የተመረጡ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር ዜጎችን “እንኳን ደስ አላችሁ” እያሉ መሆኑ  ተገልጿል፡፡

በዛሬው እለትም ለልዑካን ቡድኑ በስካይ ላይት ሆቴል የማበረታቻ ሽልማትና የእውቅና መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ተጠቁሟል፡፡

በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው 19ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ6 ወርቅ፣ 5 የብር እና1 የነሐስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.