በሽር አል አሳድ ለአራተኛ ጊዜ የሶሪያ ፕሬዚዳንት በመሆን ቃለ-መሀላ ፈፀሙ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶሪያው ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ለአራተኛ ጊዜ ለቀጣይ ሰባት ዓመታት ሀገሪቱን በፕሬዚደንትነት ለመምራት ዛሬ ቃለ-መሃላ ፈጽመዋል፡፡
የቃለ-መሃላ ሥነ-ሥርዓቱ ደማስቆ ከተማ ከሚገኘው ቤተ መንግስት በቀጥታ በሀገሪቷ የቴሌቪዥን ጣቢያ መተላለፉ ተገልጿል፡፡
በቃለ መሃላ ሥ-ነ ስርዓቱ ላይ የሀገሪቱ የሃይማኖት አባቶች ፣ የፓርላማ አባላት ፣ የፖለቲካ ሰዎች እና የጦር መኮንኖች መገኘታቸውም ነው የተነገረው።
የ55 ዓመቱ በሽር አል አሳድ በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ 95 ነጥብ 1 የህዝብ ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸው ተገልጿል።
ለመምረጥ ካርድ ከወሰዱት 18 ሚሊየን የሀገሪቷ ዜጎች ውስጥ 14 ሚሊየን ያህሉ መምረጣቸውም ነው የተገለጸው።