Fana: At a Speed of Life!

በቀጣዩ ምርጫ ሰብአዊ መብት የፖለቲካ ፖርቲዎች ዋነኛ አጀንዳ ሊሆን ይገባል – የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በስድስተኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሰብአዊ መብት የፖለቲካ ፖርቲዎች ዋነኛ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ።

ኮሚሽኑ “ሰብአዊ መብት በምርጫ ወቅት” በሚል ሀሳብ ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ እየመከረ ነው።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ከወራት በኋላ በሚካሄደው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሰብአዊ መብት ዋና አጀንዳ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ኮሚሽኑ በምርጫው ላይ ሶስት ዋና ጉዳዮች እንደሚያሳስቡትም በመድረኩ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የዜጎች የምርጫ ውስጥ ተሳትፎ መከበር፣ በምርጫው ሂደት ልዩ ትኩረት የሚሹ ዜጎች ጉዳይ እና የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ዜጎች የምርጫ ተሳትፎ ኮሚሽኑ ከሚያሳስቡት ጉዳዮች መካከል መሆኑን አንስተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.