Fana: At a Speed of Life!

በቂ የምግብ ዋስትና አለመኖር ያለጊዜ የመሞት እድልን  ይጨምራል-ጥናት

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቂ የምግብ ዋስትና አለመኖር ያለጊዜ የሚከሰት ሞትን እንደሚጨምር  አንድ ጥናት አመለከተ ፡፡

ጥናቱ የምግብ ዋስትና አለማረጋገጥ ወይንም  በቂ ምግቦችን ለማግኘት ገንዘብ አለሞኖር ያለእድሜ ለሚከሰት ሞት ምክንያት መሆኑን  ይፋ አድርጓል፡፡

በካናዳ የተጠናው ይህ  ጥናት ከፈረንጆቹ  2005 እስከ 2017 ባለው ጊዜ ውስጥ በካናዳ በሚኖሩ ከ510 ሺህ በላይ ጎልማሳዎች የተሳተፉ ሲሆን በዚህም 25 ሺህ ያህል ሰዎች ያለ ዕድሜ መሞታቸውን ጥናቱ ተመላክቷል፡፡

ጥናቱ እንዳመለከተው በቂ ምግብ ከሚያገኙ አዋቂዎች ጋር ሲነፃፀር የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ሰዎች ከ 10 በመቶ እስከ 37 በመቶ  የሚሆኑት ከካንሰር በስተቀር በማንኛውም ምክንያት ቀደም ብለው እንደሚሞቱም አረጋግጧል፡፡

በተላላፊ በሽታዎች ፣ ድንገት በሚከሰቱ አደጋዎች እና ራስን በማጥፋት ከሌሎች ጋር ሲነጻጸር  የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ሰዎች  ላይ በሁለት እጥፍ ከፍተኛ መሆኑንም ጥናቱ አመልክቷል፡፡

በምግብ ዋስትና እጦት ያለ ዕድሜያቸው የሚሞቱት አዋቂዎች  የምግብ ዋስትናቸው አስተማማኝ ከሆኑት ጋር ሲነጻጸር በ9 ዓመት ቀድመው እንደሚሞቱ ነው የተጠቆመው፡፡

ምንጭ፡-ዩ ፒ አይ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.