Fana: At a Speed of Life!

በቅርቡ እጃቸውን የሰጡት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴር ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ እጃቸውን የሰጡት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴር ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ አዲስ አበባ ገቡ።

የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የነበሩ እና በጡረታ በክብር ተሰናብተው የጁንታውን ታጣቂ ኃይል ሲመሩ እና ሲያዋጉ ቆይተው በቅርቡ እጃቸውን የሰጡት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴር ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ አዲስ አበባ ገብተዋል።

መኮንኖቹ በጡረታ ከተገለሉ በኋላ ጁንታውን በመቀላቀል የጦርነት ዝግጅት ሲያደርጉ ነበር ተብሏል።

የአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ ላይ የህወሓት ጁንታ ጥቃት በፈጸመበት ወቅትም ዋና አስተባባሪ የነበሩ መሆናቸው መገለጹን ኢብኮ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.