Fana: At a Speed of Life!

በቅርቡ ይፋ በሚደረገው የመመርመሪያ መሳሪያ የኮሮና ቫይረስ ውጤትን በደቂቃዎች ውስጥ ማወቅ ይቻላል – የዓለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት በቅርቡ ይፋ የሚያደርገው የኮሮና ቫይረስ የመመርመሪያ መሳሪያ በደቂቃዎች ውስጥ ውጤትን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የድርጅቱ ዳይሬክተር ጄነራል ቴድሮስ አድሓኖም÷ ቫይረሱን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት አዲሱ መመርመሪያ መልካም ዜና ይዞ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

መመርመሪያው በአነስተኛ ወጪና በጥቂት የህክምና መሳሪያ ውጤቱን ከ15 እስከ 30 ደቂቃ ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግ ነው የተገለጸው፡፡

ለሦስተኛው ዓለም አገራትና መካከለኛ ገቢ ላይ ለሚገኙ አገራትም ትልቅ እፎይታ ነው ተብሏል፡፡

ምክንያቱም አዲሱ መመርመሪያ የጤና ባለሙያዎች እጥረት በሚታይባቸው ቦታዎች የሚፈጠረውን ክፍተት እንደሚሞላ በመታመኑ ነው ተብሏል፡፡

እንዲሁም የመመርመሪያ መሳሪያዎች አነስተኛ በሆነባቸው አገራትም ትልቅ ሚና ይጫወታል ነው የተባለው፡፡

ከዚያም ባለፈ አሁን ይፋ የሆነው የመመርመሪያ መሳሪያ የሰውነት የመከላከል አቅም የሆነውን አንቲጅንን እንዲሁም በቫይረሱ ዙሪያ ያላውን ፕሮቲንን ይለያል ተብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ውስብስብ የሆነ የህክምና መሳሪያ ያስፈልገው የነበረውን የፒሲአር መመርመሪያ መሳሪያን እንደሚያስቀርም ኢቭኒንግ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.