Fana: At a Speed of Life!

በባህርዳር ከተማ በእሳት አደጋ በ22 የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 3 በተለምዶ ጉዶባህር ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በደረሰ የእሳት አደጋ በ22 የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ደረሰ።
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር አሰፋ ንጉሴ ÷ ቃጠሎው እንጀራ ከሚጋገርበት ወቅት ከተቀጣጣይ ነገሮች የተነሳ መሆኑን አስረድተዋል።
በቃጠሎው የ22 አባወራና እማወራ የመኖሪያ ቤት የወደመ መሆኑን የገለፁት ኢንስፔክተሩ÷ በገንዘብ ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መቃጠሉንም ተናግረዋል።
ቤቶቹ ተጠጋግተው መሰራታቸው ለቃጠሎው መባባስ ምክንያት መሆኑንም ዋና ኢንስፔክተሩ አንስተዋል ።
ቤታቸው የተቃጠለባቸው ነዋሪዎች ቃጠሎው ከቀኑ 7:00 ሰአት ገደማ መነሳቱን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ቤት እና ንብረታቸው በቃጠሎው የወደመባቸው ነዋሪዎች መንግስት የዕለት ደራሽ ምግብ እንዲያቀርብላቸው ጠይቀዋል።
በናትናኤል ጥጋቡ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!በ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.