Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የህዝብ ለህዝብ ውይይት እያደረጉ ነው

አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር ከተማ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የህዝብ ለህዝብ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡

ውይይቱ “የተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓትና ዴሞክራሲ ለህዝቦች መተሳሰብና አብሮነት ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ ያለው፡፡

በውይይቱ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ ምሁራን፣ የማህበረሰብ ተወካዮች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ማህበረሰብ አንቂዎች ተገኝተዋል፡፡

ውይይቱ በዋናነት የፖለቲካ ስርአት አመጣጥና ዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ፣ ከለውጡ ማግስት በታዩ ተግዳሮችና የህዝቦች ግንኙነት ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የህብረተሰቡ በባለቤትነት መንፈስ አስተዋጽኦ ማበርከት በሚችልባቸው አግባቦች ዙሪያም ይመክራል፡፡

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ምሁር ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው መድረኩ ልዩነቶችን አስጠብቆ በአንድ ለመኖር የሚያስችል እሳቤን መሰረት አድርጎ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችና ከሁሉም አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በአንድነት ምክክር እንዲያደርጉ ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ህዝባዊ መድረክ መሆኑንም አንስተዋል።

መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በምሁራን ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል፡፡
በትዝታ ደሳለኝ

በናትናኤል ጥጋቡ እና ትዝታ ደሳለኝ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.