Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር የባህል ሙዚቃ፣ የታንኳና ስፖርት ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጥርን በባህር ዳር የተሰኘ የባህል ሙዚቃ፣ ታንኳና ስፖርት ፌስቲቫል ያካተተ ዝግጅት በባህር ዳር ሊካሄድ መሆኑን የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው ሀላፊ አቶ አብረሃም አሰፋ እንደተናገሩት የባህርዳር ከተማ ትልቅ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸው የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገር ጎብኚዎች በየዓመቱ የሚጎበኟት በመሆኑ በጥር የሚካሄደው ሁነት የጎብኚዎችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው፡፡

በዚህ ሁነት የታንኳ ቀዘፋ የጀልባ ትርኢት የሚካሄድ ሲሆን÷ ይህ ዝግጅት የጎብኚዎችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም ከተማዋ ከቱሪዝም ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ያስችላል ብለዋል፡፡

በመሆኑም የታንኳ ቀዛፊዎች፣ የግልና የድርጅት የጀልባ ባለንብረቶች አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራ እንዲያጠናቅቁና ሌሎች የግልና የመንግስት ተቋማት እንዲሁም የከተማዋ ማህበረሰብ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የመምሪያው ሀላፊ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በ2010 ዓ.ም መከበር የጀመረው ፌስቲቫሉ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ከጥር 10 እስከ ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ከባህርዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.