Fana: At a Speed of Life!

በባሕር ዳር ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት የተከማቸ 11 በርሜል ነዳጅ እና ቤንዚን ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በጣና ክፍለ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት የተከማቸ 11 በርሜል ነዳጅ እና ቤንዚን ተያዘ።

ትናንት በሕዝብ በደረሰ ጥቆማ መሰረት የባሕር ዳር ከተማ ንግድ መምሪያ፣ የጣና ክፍለ ከተማ ንግድ ጽሕፈት ቤት፣ የከተማዋ የፀጥታ ኃይል እና ፖሊስ በጋራ ባደረጉት ዘመቻ በህገ ወጥ መንገድ የተከማቸ ነዳጅ እና ቤንዚን ተይዟል፡፡

በጣና ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ 11 በርሜል ነዳጅ እና ቤንዚን እንዲሁም ለጥቁር ገበያ የተዘጋጀ ቤንዚን በ20 ባለሁለት ሊትር የውኃ ማሸጊያ ሃይላንድ መያዙን በባሕር ዳር ከተማ ፖሊስ መምሪያ የ6ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የማኅበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ንብረት ተፈራ ገልጸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ተብሏል፡፡

የተያዘው ነዳጅ እና ቤንዚን የዘርፉ ፈቃድ በሌለው ግሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው ያሉት ምክትል ኢንስፔክተር ንብረቱ ለጥቁር ገበያው መበራከት ምክንያት የሆነውን እጥረት መፍታት ወደ ገበያ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ሕዝቡ ተመሳሳይ ጥቆማዎችን በመስጠት ከፖሊስ ጎን እንዲቆም ጥሪ ማቅረባቸውን አብመድ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.